ለኢትዮጵያ ከ18 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ዝግጅት የተጫዋቾች ጥሪ ተደረገ

በኬንያ አስተናጅነት ለሚደረገው የሴካፋ ከ18 ኣመት በታች ሴቶች ውድድር ዝግጅት ለ34 ተጫዋቾች ጥሪ ተደረገ

የኢትዮጵያ ከ18 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከሰኔ 17 እስከ ሐምሌ 1 በኬንያ አስተናጋጅነት በሚካሄደው የሴካፋ ከ18 ዓመት በታች ሴቶች ሻምፒዮና ላይ ተሳታፊ መሆኑ ሲገለፅ አምና ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድኑን ሲያሰለጥኑ የነበሩት እንዳልካቸው ጫካ ቡድኑን እንደሚመሩ ፌዴሬሽኑ አስታውቋል።

በስብስቡ በአመዛኙ ከ17 ዓመት በታች ዓለም ዋንጫ ማጣርያ ላይ ተሳታፊ የነበረው የአምናው ቡድን ላይ የነበሩ ተጫዋቾች ሲካተቱ የሴቶች ከፍተኛ ሊግን በከፍተኛ ጎል አስቆጣሪነት ያጠናቀቀችው ማህሌት ምትኩን ጨምሮ ትሩ አቋም ያሳዩ ተጫዋቾች ተካተዋል።

\"\"

ከሰኞ ግንቦት 28 ጀምሮ ዝግጅት እንደሚጀምር የተገለፀው ቡድኑ የተጫዋቾች ዝርዝር ይህንን ይመስላል፦

ግብ ጠባቂዎች

አበባ አጂቦ (አካዳሚ)
ሮማን አምባዬ (አካዳሚ)
በረከት ዘመድኩን (ቅዱስ ጊዮርጊስ)
ሊንጎ አማን (ቦሌ)

ተከላካዮች

ትርሲት ወንድወሰን (ቦሌ)
መሰረት ማሞ (አዲስ አበባ)
ሰናይት ሸጎ (አዳማ)
ቃልኪዳን ቅንበሸዋ (ቦሌ)
ፀሐይነሽ ጅሎ (ሀዋሳ)
መታሰብያ ክፍሌ (ይርጋጨፌ ቡና)
ቤተልሔም አስረሳኸኝ (ኤሌክትሪክ)
ትዝታ ኃይለማርያም (አርባምንጭ)
ባዩሽ ከምባ (ሲዳማ ቡና)
ሕይወት አመንቴ (ይርጋጨፌ ቡና)

\"\"

አማካዮች

ቤተልሔም ግዛቸው (አርባምንጭ)
ብዙዓየሁ ፀጋዬ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)
ትሁን አየለ (መቻል)
ደራ ጎሳ (አዳማ ከተማ)
ሒሩት ተስፋዬ (ቦሌ)
ፍሬሕይወት ዮሐንስ (ሀምበርቾ)
ቤተልሔም መንተሎ (አዲስ አበባ ከተማ)
ተስፋነሽ አዳነ (ቂርቆስ)

አጥቂዎች

እሙሽ ዳንኤል (ሀዋሳ)
ህዳአት ካሡ (ልደታ)
መሠረት ወርቅነህ (አርባምንጭ)
ትንቢት ሳሙኤል (ኤሌክትሪክ)
ሰለማዊት ጎሣዬ (ኤሌክትሪክ)
ዳግማዊት ሰለሞን (ይርጋጨፌ ቡና)
ቁምነገር ካሣ (ሀዋሳ)
እየሩስ ወንድሙ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)
ዓይናለም ዓለማየሁ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)
ማሕሌት ምትኩ (አካዳሚ))
ሰናይት ሁራጎ (ሲዳማ)
ሊዲያ ጌትነት (ድሬዳዋ ከተማ)