ወላይታ ድቻ አማካይ አስፈርሟል

ከሰዓታት በፊት ባዬ ገዛኸኝን ያስፈረሙት ወላይታ ድቻዎች አማካይ ወደ ስብስባቸው ቀላቅለዋል።
\"\"
በቀጣዩ የውድድር ዓመት በአሠልጣኝ ያሬድ ገመቹ የሚመሩት ወላይታ ድቻዎች የነባር ተጫዋቾቻቸውን ውል ማደስ ከጀመሩ በኋላ አሁን ደግሞ አዳዲስ ተጫዋቾችን ማስፈረም ጀምረዋል። በዚህም ባዬ ገዛኸኝን ያስፈረመ ሲሆን አሁን ደግሞ አማካይ ወደ ቡድኑ ቀላቅሏል።
\"\"
ቡድኑን የተቀላቀለው ተጫዋች አብነት ደምሴ ነው። ከወላይታ ድቻ የተገኘው ተጫዋቹ በፌዴራል ፖሊስ እና በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ቆይታ በቋሚነት ቆይታ ያደረገ ሲሆን በውሰት ውልም በኢትዮጵያ ቡና መለያ ግልጋሎት ሰርቶ የነበረ ሲሆን እንደ መጀመሪያው ፈራሚ ባዬ ወደ ቀድሞ ክለቡ ተመልሷል።