ሲዳማ ቡና የወሳኝ ተጫዋቹን ውል አድሷል

ቁመታሙ ተከላካይ በሲዳማ ቡና ቤት የሚያቆየውን የሁለት ዓመት ውል በዛሬው ዕለት ፈርሟል።
\"\"
በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ ተሳታፊ የሆነው ሲዳማ ቡና በአሰልጣኝ ሥዩም ከበደ እየተመራ ለቀጣዩ የውድድር ዘመን ክለቡን ለማጠናከር ደስታ ዮሐንስን የመጀመሪያ አዲስ ፈራሚው ማድረጉ የሚታወስ ሲሆን በዛሬው ዕለት ደግሞ ውሉ ተጠናቆ የነበረውን የቁመታሙን የመሐል ተከላካይ ጊት ጋትኩትን ኮንትራት ለተጨማሪ ሁለት ዓመት አራዝሞለታል።
\"\"
አዲስ አበባ ከተማን ከለቀቀ በኋላ ከ2011 ጀምሮ በሲዳማ ቡና መለያ ያለፉትን አምስት ዓመታት ያሳለፈው ተከላካዩ ለቀጣዮቹ ሁለት ተጨማሪ ዓመታትም በክለቡ ለመቆየት ፊርማውን ዛሬ አኑሯል።