ሁለት የብሔራዊ ቡድኑ አባላት ወደ አሜሪካ አይጓዙም

ከቀናት በኋላ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወደ አሜሪካ በሚያደርገው ጉዞ ሁለት የቡድኑ አባላት እንደማይጓዙ ታውቋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወደ አሜሪካ ተጉዞ ለሚያደርጋቸው ሁለት የወዳጅነት ጨዋታዎች ለ24 ኢትዮጵያዊ እና ለ4 ትውልደ ኢትዮጵያዊ ተጫዋቾች ጥሪ መደረጉ ይታወቃል። ጥሪ ከተደረገላቸው ተጫዋች መካከል ዳዋ ሁቴሳ እና ከአሠልጣኝ ቡድን አባላት ደግሞ ምክትል አሠልጣኙ ደግአረገ ይግዛው ወደ አሜሪካ እንደማይጓዙ ታውቀቋል።
\"\"
ዳዋ በመጀመርያው የብሔራዊ ቡድኑ ልምምድ የተገኘ ቢሆንም ከትናትና ጀምሮ ከቡድኑ ጋር አብሮ ልምምድ እንዳልሰራ ታውቋል። በተጨማሪም አሰልጣኝ ደግአረገ ይግዛውም ከመጀመርያው የዝግጅት ወቅት ጀምሮ ከቡድኑ ጋር እንደማይገኙ አስቀድመን መግለፃችን ሲታወቅ ሁለቱም ወደ አሜሪካ ያለመጓዛቸው ምክንያት ቪዛ ባለማግኘታቸው መሆኑን ሰምተናል።
\"\"
ብሔራዊ ቡድኑ አሜሪካ በሳምንቱ መጨረሻ የሚያቀና ሲሆን በዋሺንግተን ዲሲ ከጉያና ጋር እንዲሁም በአታላንታ ከአታላንታ ሮቨርስ ጋር የወዳጅነት ጨዋታውን እንደሚያደርግ ይታወቃል።