የጦና ንቦቹ አጥቂ አስፈርመዋል

በዛሬው ዕለት ወደ ዝውውሩ የገቡት ወላይታ ድቻዎች አጥቂ አስፈርመዋል።
\"\"
የዘንድሮ የውድድር ዓመት ከተጠናቀቀ በኋላ ወዲያው አሠልጣኝ ያሬድ ገመቹን በመንበሩ የሾሙት ወላይታ ድቻዎች የግብ ጠባቂያቸው ቢኒያም ገነቱን እና ተከላካያቸው መልካሙ ቦጋለን ውል ማደሳቸውን ይፋ አድርገን ነበር። ሶከር ኢትዮጵያ አሁን ባገኘችው መረጃ መሠረት ደግሞ የአጥቂ መስመር ተጫዋቹ ባዬ ገዛኧኝን አስፈርመዋል።
\"\"
የቀድሞ የስልጤ ወራቤ፣ መከላከያ ፣ ሲዳማ ቡና፣ ወላይታ ድቻ እና ባህር ዳር ከተማ ተጫዋች ያለፉትን ሁለት የውድድር ዓመታት በሀዲያ ሆሳዕና ቆይታ ካደረገ በኋላ ዳግም ወደ ቀድሞ ክለቡ ወላይታ ድቻ አምርቷል።