ቅዱስ ጊዮርጊስ የግብ ጠባቂውን ውል አድሷል

የፈረሰኞቹ የወጣት ቡድን ፍሬ የሆነው ግብ ጠባቂው ባህሩ ነጋሽ ለሁለት ተጨማሪ ዓመት ውሉን አራዝሟል።
\"\"
ከአዳዲስ ተጫዋቾች በፊት የነባር ተጫዋቾቹን ውል ከቀናት በፊት ማደስ የጀመሩት ቅዱስ ጊዮርጊሶች የግብ ጠባቂው ባህሩ ነጋሽን ውል ለተጨማሪ ሁለት ዓመት አሪዝሟል።
\"\"
ከክለቡ ከ20 ዓመት በታች ቡድን ካደገ በኋላ ያለፈትን አራት ዓመታት በዋናው የፈረሰኞቹ ቤት ግልጋሎት ሲሰጥ የነበረው ግብ ጠባቂው ከናትናኤል ዘለቀ ፣ ከበረከት ወልዴ እና አማኑኤል ተርፉ ቀጥሎ አራተኛው ውል ያራዘመ ተጫዋች ሆኗል።