አማኑኤል ገብረሚካኤል ወደ ኢትዮጵያ ተመልሷል

በደቡብ አፍሪካው ክለብ የአስራ ስድስት ቀናት የሙከራ ቆይታን ያደረገው አጥቂው ትላንት አመሻሽ ወደ ሀገሩ ተመልሷል።

የ2015የኢትዮጵያ ፕሪሞየር ሊግን ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ሻምፒዮን በመሆን ካጠናቀቀ በኋላ ለሙከራ ሐምሌ 2 ወደ ደቡብ አፍሪካው ሞሮካ ስዋሎስ አምርቶ የነበረው አጥቂው አማኑኤል ገብረሚካኤል ከአስራ ስድስት ቀናት የሙከራ ቆይታ በኋላ ትላንት አመሻሽ ወደ ሀገር ውስጥ መመለሱን ተጫዋቹ በተለይ ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር በነበረው ቆይታ ተናግሯል።
\"\"
ከዳሽን ቢራ የእግር ኳስ ህይወቱን ከጀመረ በኋላ በመቐለ 70 እንደርታ እንዲሁም ያለፉትን ሁለት የውድድር ዘመናት በፈረሰኞቹ መለያ ከክለቡ ጋር የሊግ ዋንጫን ያሳካው ተጫዋቹ ከዘንድሮው ፕሪምየር ሊግ መጠናቀቂያ ማግስት ወደ ደቡብ አፍሪካ አምርቶ በሞሮካ ስዋሎስ ያለፉትን ሁለት ሳምንታት በክለቡ የሙከራ ጊዜን አሳልፎ ትላንት አመሻሽ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሷል። ተጫዋቹ ከክለቡ የቀረበለት የኮንትራት ጊዜ ማነስ እና ጥቅማጥቅምቹም አመርቂ አለመሆናቸውን ተከትሎ ስለ መመለሱ ነግሮናል።
\"\"
ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር እንደማይቀጥል ያረጋግጥነው ተጫዋቹ በቀጣይ ወደየት እንደሚያመራ በይፋ ባይገልፅልንም ፋሲል ከነማ ተጫዋቹን የማግኘት ዕድሉ የሰፋ መሆኑን ዝግጅት ክፍላችን ያገኘችው መረጃ አመላክቷል።