መድን የሁለት ተጫዋቾችን ውል አድሷል

ቡድኑን እያጠናከረ የሚገኘው ኢትዮጵያ መድን የአጥቂ እና የተከላካይ መስመር ተጫዋቾቹን ውል ለተጨማሪ ዓመት አራዝሟል።
\"\"
በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አድጎ 3ኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው ኢትዮጵያ መድን እስካሁን የአራት አዳዲስ ተጫዋቾችን ዝውውር ማጠናቀቁ ይታወቃል። ከአዳዲስ ተጫዋቾች በተጨማሪ የአምበሉ አብዱልከሪም መሐመድን ውል ከቀናት በፊት ያራዘመው ክለቡ አሁን ደግሞ የሌሎች ሁለት ተጫዋቾችን ውል ማራዘሙ ታውቋል።

ውሉን ያራዘመው የመጀመሪያው ተጫዋች ተካልኝ ደጀኔ ነው። ዓምና ከአርባምንጭ ከተማ ቡድኑን ተቀላቅሎ ግልጋሎት ሲሰጥ የነበረው የመስመር ተከላካዩ በክለቡ እንደሚቀጥል እርግጥ ሆኗል።
\"\"
ሌላኛው ተጫዋች ደግሞ ያሬድ ዳርዛ ነው። የአጥቂ መስመር ተጫዋቹ በሊጉ 362 ደቂቃዎችን ዘንድሮ የተጫወተ ሲሆን ሁለት ግቦችንም ከመረብ አሳርፏል። እርሱም እንደ ተካልኝ በክለቡ ለተጨማሪ ዓመት ለመቆየት ስምምነት ፈፅሟል።