ከፍተኛ ሊግ | ጋሞ ጨንቻ በርካታ ተጫዋቾችን አስፈርሟል

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ተወዳዳሪው ጋሞ ጨንቻ የአስራ ሦስት አዳዲስ ተጫዋቾችን ዝውውር ፈፅሟል።

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ላይ በተከታታይ ዓመታት ጠንካራ ተፎካካሪ በመሆን በሊጉ ይታይ የነበረው ጋሞ ጨንቻ ለ2016 የውድድር ዘመን ቀደም ብሎ የቀድሞው የክለቡን አሰልጣኝ ማቲያስ ለማን በዋና አሰልጣኝነት የቀጠረ ሲሆን ቡድኑንም ለማጠናከር አሰልጣኙ በዝውውር መስኮቱ በመካፈል ወደ አስራ ሦስት የሚጠጉ አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ስብሰባቸው ቀላቅለዋል።

የክለቡ አዲስ ፈራሚ የሆኑት ተጫዋቾች ግብ ጠባቂው አቡሽ አበበ ፣ ተከላካዮቹ ሲሣይ ማሞ ፣ አያልቅበት በቀለ ፣ አማኑኤል ዋሪ እና ሞገስ ቱሚቻ አማካዮቹ ለገሠ ዳዊት ፣ ታደለ ፈለቀ ፣ ዘኪ አብዱላሂ እና የትምጌታ ታደሠ እንዲሁም አጥቂዎቹ ያሬድ መኮንን ፣ ፍሬው ዓለማየሁ ፣ ምንተስኖት ታምሬ እና ፋሲካ አለኝታ መሆናቸው ታውቋል።

በምድብ ለ የተደለደለው ጋሞ ጨንቻ ነገ 10:00 ላይ ከከፋ ቡና ጋር በሚያደርገው ጨዋታ የውድድር ዓመቱን ይጀምራል።