ከፍተኛ ሊግ | የካ ክፍለ ከተማ ራሱን በዝውውር አጠናክሯል

በከፍተኛ ሊጉ ምድብ ለ ስር ተደልድሎ የሚገኘው የካ ክፍለ ከተማ የአዳዲስ ተጫዋቾችን ዝውውር አገባዷል።

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ላይ ረዘም ያለ የተሳትፎ ቆይታን እያደረገ የሚገኘው የካ ክፍለ ከተማ በዘንድሮው የሊጉ ቆይታውን ክፍተት አለብኝ ባላቸው ቦታዎች ላይ በአሰልጣኝ ባንተይርጋ ጌታቸው መሪነት አዳዲስ ተጫዋቾችን በማስፈረም ቡድኑን ስለ ማጠናከሩ ክለቡ ለዝግጅት ክፍላችን በላከው መረጃ አመላክቷል።

አዳዲስ ፈራሚዎቹን ስንመለከት በግብ ጠባቂነት ለይኩን ነጋሽ እና ሳሙኤል ደረጀ ፣ ተከላካዮች ዘላለም ፍቃዱ ፣ በረከት አድማሱ ፣ ወርቁ አዲስ እና ሚኪያስ ታምራት ፣ አማካዮች ክብሮም ፅድቁ እና ታከለ ታንቱ አጥቂዎች ጁንዴክስ አወቀ ፣ ናትናኤል ሌሊሳ ፣ አንተነህ ተሻገር ፣ ተካልኝ ገብረሥላሴ እና ደረጀ ነጋሽ ሆነዋል።

የካ ክፍለ ከተማ ነገ 08:00 ላይ ከደሴ ከተማ ጋር በሚያደርገው ጨዋታ የውድድር ዓመቱን ይጀምራል።