ከፍተኛ ሊግ | ወልዲያ የአዳዲስ ተጫዋቾችን ዝውውር አጠናቋል

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ላይ የሚካፈለው ወልዲያ የአስር አዳዲስ ተጫዋቾችን ዝውውር ሲቋጭ የነባሮችን ውልም አራዝሟል።

ከኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ከወረደ በኋላ በከፍተኛ ሊጉ ላይ ተሳትፎን እያደረገ የሚገኘው ወልዲያ ለ2016 የውድድር ዘመን ተሳትፎውን በተሻለ ተፎካካሪ ለመሆን በማሰብ የአሰልጣኝ ካሊድ መሐመድን ውል ያራዘመ ሲሆን በኢትዮጵያ ዋንጫ ላይ ተሳትፎን አድርጓል። ቡድኑ ራሱን ለማጠናከር የአስር አዳዲስ ተጫዋቾችን ዝውውር ሲቋጭ የአስራ ሦስት ነባሮችን ውል ስለማራዘሙ ለሶከር ኢትዮጵያ በላከው ዝርዝር መረጃ አመላክቷል።

አዲስ ፈራሚዎችን ስንመለከት የቀድሞው የሀላባ ከተማ ግብ ጠባቂ ስንታየሁ ታምራት ፣ በደሴ ከተማ የነበረው ግብ ጠባቂ እስራኤል አለ ፣ ከሱሉልታ የተቀላቀለው ቴዎድሮስ እንዳለ ፣ በቤንች ማጂ ቡና ሲጫወት የቆየው ተከላካይ ፉዓድ ነስሮ ፣ የቀድሞው የኮልፌ ፣ የሲዳማ እና ወልቂጤ የመስመር አጥቂ የነበረው አንዋር ዱላ ፣ በሀዲያ ሆሳዕና እና ሀምበሪቾ የተጫወተው መስቀሉ ለቴቦ ፣ በኃይሉ ተስፋዬ አጥቂ ፣ በዱራሜ የነበረው አማካይ አለኝታ ማርቆስ ፣ በአቃቂ ቃሊቲ ቆይታ የነበረው ሊዮናርዶ ሰለሞን እና በአቃቂ ቃሊቲ የነበረው ተከላካይ ፉዓድ ጀማል ሆነዋል።

ወልዲያ ነገ 04:00 ላይ ከጅማ አባ ጅፋር ጋር የምድብ ሀ የመክፈቻ ጨዋታን ያከናውናል።