የአዳማ ከተማ ተጫዋች ወደ ቡልጋሪያ አቅንቷል

“የባቡር ተጓዦቹ” ለተከላካይ አማካዩ የሙከራ ዕድል አመቻችተዋል።

የውድድር ዓመቱን ከአዳማ ከተማ ጋር ያሳለፈው ናይጀርያዊው ቻርለስ ሪባኑ በቡልጋርያ የመጀመርያ የሊግ እርከን በሚሳተፈው ሎኮሞቲቭ ፕሎቭዲቭ የሙከራ ዕድል አግኝቷል። የተጫዋቹን እንቅስቃሴ በተንቀሳቃሽ ምስልና በመልማዮቹ አማካኝነት መመልከቱን ከገለፀ በኋላ ለአማካዩ የሰላሣ ቀናት የሙከራ ዕድል እንደሰጠው የገለፀው ክለቡ የተጫዋቹን ሙሉ ወጪ እንደሚሸፍንም አያይዞ ገልጿል።

ወደ ኢትዮጵያ ከመጣ በኋላ በሀምበሪቾ፣ አዲስ አበባ ከተማ፣ ባህር ዳር ከተማ እና አዳማ ከተማ መጫወት የቻለው ይህ የተከላካይ አማካይ በትናንትናው ዕለት ወደ ስፍራው ያቀና ሲሆን በተሰጡት ሰላሣ ቀናት ጥሩ ብቃት ካሳየ በቋሚነት የቡድኑ ተጫዋች ይሆናል።