ብሄራዊ ሊጉ የሚጀመርበት ቀን በድጋሚ ተራዘመ

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሊግ የ2009 የውድድር ዘመን የሚጀመርበት ቀን ለ3ኛ ጊዜ ተራዝሟል፡፡

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የውድድሩ ተሳታፊ ክለቦች መክፈል የሚጠበቅባቸውን የዳኞች እና ታዛቢዎች ክፍያ ባለማጠናቀቃቸው ሊጉ የሚጀመርበት ቀን ወደ ታህሳስ 2 ቢሸጋገርም አሁንም ክለቦች ክፍያ ባለማጠናቀቃቸው በድጋሚ ለታህሳስ 8 እንዲሸጋገር ተደርጓል፡፡ ፌዴሬሽኑ ባደረገው ውይይት ውድድሩ ከዚህ በኋላ እንደማይራዘምና ክፍያውን ባጠናቀቁ ክለቦች መካከል ለመጀመር እንዳሰበ ታውቋል፡፡

በውድድሩ ላይ ከሚሳተፉ ክለቦች መካከል አንዳንዶቹ መፍረሳቸው የተነገረ ሲሆን የመሳተፍ አለመሳተፍ ውሳኔዎችን እስካሁን ያላሳወቁ ክለቦች መኖራቸውም ታውቋል፡፡ በፈረሱ ክለቦች ምትክም አዳዲስ ክለቦች እንዲካተቱ ለማድረግ እየተሞከረ እንደሆነ ተሰምቷል፡፡

2 thoughts on “ብሄራዊ ሊጉ የሚጀመርበት ቀን በድጋሚ ተራዘመ

  • December 8, 2016 at 7:08 am
    Permalink

    በቃ እግር ዃስን የማይደግፉ የስራ አመራሮች በስሜት አልባነት በሚወስኑት ውሳኔ የብዙ ተስፈኞች ወጣት ከስሞና ሞቶ መቅረት አለበት መተሀራ እኮ ለ ሀገራችን እግር ዃስ ጀግና የሆኑ ተጫዎቾችን ያፈራ ቡድን ነው ሀሰን በሽር ሰለሞን ገብረ መድን ይሁን እንደሻው ብሩክ ቀልቦX እና ሌሎች ብዙ ብቃት ያላቸው ተጫዋቾችን ለብሔራዊ ቡድን የጫወተ ነው አውን ግን ለ መፍረስ ከ ጫፍ ደርሷል በጀት የለም በሚል ምክንያት መተሀራን ከመበተን እና ከ መፍረስ የእስፖርት ጋዜጠኞች የበኩላቹን ሚና ተጫወቱ እባካቹ

  • December 8, 2016 at 6:54 am
    Permalink

    betam yasazenale wenji ferese awen demo methara yemeferese adega lay new are lemanew abete yemebalew beka ande bale seletane eger kase kalewedede ye bezu wetatoche hiyewet yebelashe malete new

Leave a Reply

error: