አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ በወላይታ ድቻ ውላቸውን አደሱ

የኢትዮጵያ ዋንጫ ቻምፒዮኑ ወላይታ ድቻ የአሰልጣኙ መሳይ ተፈሪን ውል ለተጨማሪ ሁለት የውድድር ዘመናት ለማደስ ከስምምነት ደርሷል፡፡ አሰልጣኙ ከድቻ ጋር የተስማሙበትን የክፍያ መጠን ክለቡ ከመግለጽ ቢቆጠብም ከዚህ ቀደም ከሚያገኙት የተሻሻለ ክፍያ እንደሚያገኙ ታውቋል፡፡

ከስምምነቱ መጠናቀቅ በኋላ ለሶከር ኢትዮዽያ አስተያየታቸውን የሰጡት አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ በቀጣይ በፕሪምየር ሊጉ እና ካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ጠንካራ ተፎካካሪ ማድረግ እቅዳቸው እንደሆነ ተናግረው ለዚህ እንዲረዳቸውም ቀድሞ ከነበረው የተጫዋች ግዢ ፖሊስያቸው የተወሰነ ለውጥ እንደሚኖር ተናግረዋል።

ወላይታ ድቻ በ2001 ሲመሰረት አሰልጣኝ ተደርገው የተሾሙት የቀድሞው የአርባምንጭ ጨጨ እና ኢትዮጵያ ቡና ኮከብ መሳይ ተፈሪ ላለፉት 8 አመታት በወላይታ ድቻ የቆዩ ሲሆን ወላይታ ድቻ ከሌሎች ክለቦች በተለየ የሚመድበውን ዝቅተኛ በጀት በመጠቀም ተፎካካሪ ቡድን በመገንባት መልካም ስም አትርፈዋል፡፡

6 thoughts on “አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ በወላይታ ድቻ ውላቸውን አደሱ

 • July 14, 2017 at 10:32 am
  Permalink

  Ethiopia wusti kalu wotate aseltagnoch Wust mirtu Mesay NW wodefit bizu mesirat endmichil be WolaitaDFC asaytonal…beketyi yekontirat gizewu Melkam yesir gize yihunilt. Thanks
  Dan

 • July 13, 2017 at 6:19 pm
  Permalink

  Mesay or Anbes. Morheno
  Bawenat bante maseletene bezu lewet agenchebetalew wedehalew besay bro

 • July 13, 2017 at 4:46 pm
  Permalink

  “ቀድሞ ከነበረው የተጫዋች ግዢ ፖሊስያቸው የተወሰነ ለውጥ እንደሚኖር ተናግረዋል።” this statement is must as a team…..he deserve to be a coach for this team!!

 • July 13, 2017 at 4:12 pm
  Permalink

  የአርባምንጭ ጨርቃጨርቅ ኮከብ በሚለው ይስተካከል

Leave a Reply

error: