የክቡር ይድነቃቸው ተሰማ መታሰብያ ውድድር ምድብ ድልድል ይፋ ሆኗል

ታላቁ የእግር ኳስ ሰው ክቡር ይድነቃቸው ተሰማን ለመዘከር የሚደረገው የታዳጊዎች ውድድር የምድብ ጨዋታዎች ከመጪው ረቡዕ ጀምሮ ይከናወናል።

17 ቡድኖች በአራት ምድቦች ተከፍለው በሚያደርጉት በዚህ ውድድር ላይ በምድቦቹ ለመካተት የተደረጉ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ከሐምሌ 27 ጀምሮ ተደርገው አላፊዎቹ ታውቀዋል። ዛሬ ረፋድ ላይ ደግሞ በቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ጽ/ቤት የእጣ አወጣጥ ስነ-ስርዓቱ እንደተካሄደ የክለቡ ፌስቡክ ገፅ አስነብቧል። ድልድሉም ከታች እንደተመለከተው ሆኗል።

ምድብ ሀ

አዲስ አሰላ፣ አርባምንጭ፣ ቤተሰብ፣ የነገ ተስፋ

ምድብ ለ

ድል፣ ወረዳ 8፣ ላሜሲያ አሰላ፣ ኢትዮጵያዊነት

ምድብ ሐ

መካኒሳ፣ ENPA፣ ቂርቆስ፣ ሸኖ

ምድብ መ

አንለያይም፣ ዓለምገና፣ ጫጫ፣ ሰንዳፋ፣ ዲላ

ነሀሴ 16 በሚጀመሩት የምድብ ጨዋታዎች ከምድብ ሐ መካኒሳ ከ ሸኖ በ2፡00 እንዲሁም ENPA ከ ቂርቆስ በ3፡00 ሰዓት ሲገናኙ በመቀጠል ደግሞ በምድብ መ  አንለያይም ከሰንዳፋ በ4፡00 ሰዓት እና አለምገና ከ ጫጫ በ5፡00 ጨዋታቸውን እንደሚያደርጉ ክለቡ ጨምሮ ገልጿል።

error: