ዳዊት ፍቃዱ ወደ ወልዋሎ አምርቷል

ረቡዕ መስከረም 09 ቀን 2010

የበዝውውር መስኮቱ በርካታ ተጫዋቾች መካከል አንዱ የሆነው ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ በአመዛኙ የተከላካይ እና አማካይ መስመሩ ላይ አተኩሮ ቆይቶ ፊቱን ወደ አጥቂ ስፍራ በማዞር ዳዊት ፍቃዱን አስፈርሟል። 

ዳዊት ፍቃዱ ለ7 የውድድር ዘመናት ከቆየበት ደደቢት ለቆ በ2010 ሀዋሳን ከተቀላቀለ በኋላ በሁለተኛ ሳምንት ወልዲያ ላይ ሐት-ትሪክ ሰርቶ አጀማመሩን ቢያሳምርም በቀሪው የውድድር ዓመት የታሰበውን ያህል ጎሎችን ማስቆጠር ሳይችል ቀርቷል። የቀድሞው የአየር ኃይል እና ኢትዮጵያ ቡና አጥቂ በወልዋሎ የአንድ ዓመት ውል የተፈራረመ ሲሆን በክረምቱ ደደቢትን ለቀው ወደ ክለቡ ካቀኑ በርካታ የቀድሞ የቡድን ጓደኞቹ ጋር በድጋሚ የሚገናኝ ይሆናል።

በተያያዘ የወልዋሎ ዜና ባለፈው ሳምንት ከናይጀርያ እና ከማላዊ ለሙከራ መጥተው የነበሩት ሻሂድ ባቢንቶን እና ዲያሎ ካሮንጋ በቆይታቸው አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነ ማርያምን ማሳመን ባለመቻላቸው መሰናበታቸው ታውቋል።