ዋልያዎቹ ወደ ሐገር ቤት ሲመለሱ የሥዩም አባተን ቤተሰቦችም አፅናንተዋል

እሁድ በአራተኛ የምድብ ጨዋታ በኬንያ ከጨዋታ ብልጫ ጋር የ3-0 ሽንፈት በማስተናገድ ዳግመኛ ወደ አፍሪካ ዋንጫ የማለፍ ዕድላቸውን አጣብቂኝ ውስጥ የከተቱት ዋልያዎቹ ከናይሮቢ በመነሳት ትላንት ማምሻውን 2:00 ሰአት አዲስ አበባ ገብተዋል።

የብሔራዊ ቡድኑ አባላት ወደ ሆቴላቸው ከማቅናታቸው በፊት የፌዴሬሽኑ የስራ አስፈፃሚ አባላት፣ የፅህፈት ቤት ኃላፊው እና የቡድኑ አሰልጣኞች፣ ተጨዋቾች በመሆን ባሳለፍነው ሳምንት ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት እና ስርዓተ ቀብራቸው ወደተፈፀመው የቀድሞው ታላቅ አሰልጣኝ ሥዩም አባተ መኖርያ ቤት ተጉዘዋል። የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን በመግለፅ ቤተሰባቸውን እና ዘመድ ወዳጆቻቸውን አፅናንተው ተመልሰዋል ።


ከአንድ ሳምንት በፊት የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል የእድሜ ልክ አባል የሆኑት ዋልያዎቹ አሰልጣኝ ሥዩም ለኢትዮዽያ እግርኳስ ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋፆኦ ክብር እና እውቅና በመስጠት በመኖርያ ቤታቸው በመገኘት ይህን ሰናይ ተግባር መፈፀማቸው በመልካም ጎኑ የሚጠቀስ ነው ።

error: