የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ብሔራዊ ቡድን የመጨረሻ ልምምዱን አከናወነ

የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ነገ ከማሊ አቻው ጋር በአዲስ አበባ ስታድየም ለሚኖረው የማጣርያ ጨዋታ ዛሬ ማለዳ ላይ የመጨረሻ ልምምዱን ሰርቷል።
ከየካቲት ወር መጨራሻ ጀምሮ ዋቢ ሸበሌ ሆቴል ማረፊያውን በማድረግ ዝግጅቱን እያደረገ የሚገኘው የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ከሲሸልስ ዋናው ብሔራዊ ቡድን ጋር አዲስ አበባ ላይ ሁለት የወዳጅነት ጨዋታዎች በማድረግ አቋሙን መፈተሽ ችሏል። ከመጀመርያ ተመራጭ 34 ተጫዋቾች መካከልም አሰልጣኝ አብርሀም መብራቱ 8 ተጫዋቾችን በመቀነስ 26 ተጫዋቾችን አስቀርተው ለቀናት ልምምዳቸውን ሲሰሩ ቆይተዋል። አሁን ደግሞ የመጨረሻ ተመራጭ 23 ተጫዋቾቻቸውን ለይተው በመያዝ ሳሙኤል ተስፋዬ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ የዓብስራ ተስፋዬ (ደደቢት) እና እዮብ ዓለማየሁን (ወላይታ ድቻ) መቀነሳቸው ታውቋል።

የቀድሞው የፌስቡክ ገፃችን በኛ ቁጥጥር ስር የማይገኝ በመሆኑ አዲሱ ገፃችንን ሊንኩን በመከተል ላይ ያድርጉ – facebook.com/SoccerEthiopia

ዛሬ ከማለዳው 01:00 ጀምሮ በአዲስ አበባ ስታድየም ቀለል ያለ ልምምድ የሰራው ብሔራዊ ቡድኑ ለትምህርት ወደ ሀንጋሪ ካቀናው ምክትል አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ በስተቀር ሁሉም የቡድኑ አባላት ለነገው ጨዋታ ዝግጁ መሆናቸውን ተመልክተናል።

ጨዋታውን ናሚቢያዊያኑ ጃክሰን ፓቫዛ (ዋና) ፣ ማቲየስ ካንያንጋ እና አይዛካር ቡኢስ (ረዳቶች) ይመሩታል።

የመልሱ ጨዋታ ማክሰኞ መጋቢት 17 ማሊ ባማኮ ላይ የሚካሄድ ይሆናል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *