ወላይታ ድቻ ለጌዴኦ ተፈናቃዮች ድጋፍን አደረገ

ወላይታ ድቻ በቅርቡ ከመኖሪያ አካባቢያቸው በመፈናቀል ለችግር ለተጋለጡት የጌዲኦ ማኅበረሰብ የገንዘብ እና የእህል ድጋፍን አደረገ፡፡

ስራ አስኪያጁ አቶ አሰፋ ሆሲሶ ለሶከር ኢትዮጵያ እንደገለፁት ከሆነ ወላይታ ድቻ በ16ኛ ሳምንት ከስሑል ሽረ ጋር በሜዳው ነጥብ በተጋራበት ጨዋታ በእለቱ የደጋፊ ማኅበሩ ከ60 ሺህ ብር በላይ እንዲሰበሰብ ያደረጉ ሲሆን ክለቡ ደግሞ ከአንድ መቶ ሀምሳ ሺህ ብር በላይ ወጪ በማውጣት የምግብ ዱቄቶችን በመግዛት በስፍራው በመገኘት አበርክቷል፡፡

የቀድሞው የፌስቡክ ገፃችን በኛ ቁጥጥር ስር የማይገኝ በመሆኑ አዲሱ ገፃችንን ሊንኩን በመከተል ላይ ያድርጉ – facebook.com/SoccerEthiopia

አቶ አሰፋ ጨምረው ይህ የኢትዮጵያዊነት ስሜትን የሚነካ በመሆኑ እንደ አንድ ዜጋ ተሰምቶን አድርገናል ብለዋል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *