የአፍሪካ ዋንጫ ድልድል ይፋ ሆኗል

ግብፅ የምታዘጋጀው የ2019 የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ድልድል ዓርብ ምሽት በካይሮ ይፋ ሆኗል።

በሰኔ ወር አጋማሽ በግብፅ የሚጀመረው እና ለመጀመርያ ግዜ ሃያ አራት ሃገሮች የሚያሳትፈው የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ድልድሉ በካይሮ ከተማ ሲካሄድ ከወዲሁ የበርካቶች ትኩረት የሳቡ ተጠባቂ ጨዋታዎች የእግር ኳስ ማኅበረሰቡን እያነጋገሩ ይገኛሉ።

ያያ ቱሬ፣ ሬጎቤር ሶንግ፣ ሙስጣፋ ሃጂ ፣ ሳሙኤል ኤቶ እና ሌሎች በርካታ የአፍሪካ እግር ኳስ ክዋክብት በተገኙበት ካይሮ ፒራሚድ አቅራብያ በሚገኘው ጊዛ በተባለው እጅግ ማራኪ ስፍራ የተካሄደው ይህ ስነ ስርዓት ከምሽቱ ሶስት ሰዓት ጀምሮ የተካሄደ ሲሆን መጨረሻ ላይ በተደረገው የዕጣ ማውጣት ስነ ስርዓት ፍፃሜውን አግኝቷል።

በዚ መሰረት በምድብ አራት ሞሮኮ ፣ ኮትደቫር ፣ ደቡብ አፍሪካና የኢታሙና ኩሙይኒ ሀገር ናሚብያ የሚገናኙበት ምድብ የብዙዎችን ትኩረት ስቧል።

ይህ ውድድር በኢትዮጵያ አቆጣጠር ሰኔ 14 የሚጀመር ሲሆን ውድድሩ በስድስት ስቴድየሞች ይከናወናል።

የምድብ ድልድሉ ይህንን ይመስላል:-


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡