የአሰልጣኞች አስተያየት | ጅማ አባ ጅፋር 1-1 ሀዋሳ ከተማ

የጅማ አባጅፋር እና የሀዋሳ ከተማ ጨዋታ 1-1 ከተጠናቀቀ በኋላ የሁለቱ ቡድኖች አሰልጣኞች የሚከተለውን አስተያየት ሰጥተዋል፡፡

ዩሱፍ ዓሊ (ጅማ አባጅፍር)

ስለ ጨዋታው

በዛሬው ጨዋታ ማማዱ ሲዲቤ ባለመኖሩ ምክንያት ወደ 4-3-3 ቀይረን ነበር የገባነው። በመጀመሪያው አጋማሽ ኳስን ከማንሸራሸር ባለፈ ወደፊት ሄደን እድሎችን አልፈጠርንም። የዘነበውም ዝናብ ተፅዕኖ ነበረው። ከእረፍት መልስ አጨዋወታችንን ወደ 4-4-2 ቀይረን ነበር የተጫወትነው።

ስለ አጥቂዎቻቸው ጉዳት

ማማዱ ሲዲቤን ለሚቀጥለው ጨዋታ ሙሉ ለሙሉ እንዲያገግም ነው የዛሬውን ጨዋታ ያሳረፍነው። የኦኪኪ የዛሬውም ጉዳት ስብራት አይደለም የገጠመው ከሜዳ የሚያርቅ አይመስለኝም። ለሚቀጥለው ጨዋታ ሁለቱም ዝግጁ ይሆናሉ ብዬ አስባለሁ፡፡

አዲሴ ካሣ (ሀዋሳ ከተማ)

ስለ ጨዋታው

ጠንከር ያለ ጨዋታ ነበር ያደረግነው። ከሽንፈት እንደመመለሳችን ውጥረት ውስጥ ገብተን ነበር። ቀድመን ማግበረት ችለን ነበር። እነሱ በደጋፊዎችቻቸው መነሳሳት ጎሉን ያስቆጠሩት። በአጠቃላይ ጨዋታው ጥሩ ነበር

ተጫዋቾች ያቀዱትን ታክቲክ ስለመተግበራቸው

በተጫዋቾቼ ተደስቻለሁ። ተሸንፎ የመጣ ቡድን አንመስልም። ተጫዋቾቼ ላይ ባየሁት ቆራጥነት ደስተኛ ነኝ። የመጀመሪያው እቅዳችን አሸንፈን ለመውጣት ነበር። በመጀመሪያው አጋማሽ አሰቆጥረን ያስቆጠርነውን ማስጠበቅ ባለመቻላችን በሁለተኛው አጋማሽ ተቆጥሮብን አቻ ወጥተናል። ሁለተኛው እቅዳችን እኩል ለእኩል ነበር ያሰብነው፤ እቅዳችን አሳክተናል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡