ኢትዮጵያ ቡና ከኮንጓዊው አጥቂ ጋር ተለያይቷል

ሱሌይማን ሎኩዋ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር በስምምነት መለያየቱን ክለቡ አስታውቋል።

በክረምቱ የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ኢትዮጵያ ቡናን መቀላቀል የቻለው ዲ/ሪ ኮንጓዊው አጥቂ በአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ላይ ባሳየው ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴ ጥሩ የውድድር ዘመን እንደሚያሳልፍ ቢጠበቅም በጉዳት የሚጠበቀውን ግልጋሎት መስጠት ሳይችል ቀርቷል። በዚህም ከክለቡ ጋር ቀሪ ውሉን በስምምነት በመቅደድ መለያየቱ ይፋ ሆኗል።

የቀድሞው የዛናኮ አጥቂ ቡና በሊጉ ዘንድሮ ካደረጋቸው ጨዋታዎች በአስራአንዱ ላይ መሳተፍ ሲችል በድምሩ 782 ደቂቃዎችን በሜዳ ላይ ቆይቷል። ከነዚህም ውስጥ በሦስቱ ብቻ ሙሉ ጨዋታ ያደረገ ሲሆን ሁለቴ ተቀይሮ ሲገባ ስድስት ጊዜ ደግሞ ጨዋታውን ጀምሮ ተቀይሮ ወጥቷል። በነዚህ ጊዜያት ሁለት ግቦችን ያስቆጠረው ሎክዋ አንድ ግብ የሆነ ኳስም አመቻችቶ አቀብሏል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

error: