ሁለት ኢትዮጵያውያን ዳኞች ወደ አፍሪካ ዋንጫው ያመራሉ

በ2019 የአፍሪካ ዋንጫ ላይ የሚመሩ ዳኞችን ለመምረጥ በሞሮኮ ሲካሄድ የቆየውን ፈተና እና ስልጠና ሲከታተሉ የነበሩት የኢትዮጵያውያን ዳኞች የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታዎችን እንደሚመሩ ተረጋገጠ።

ከሚያዚያ 20-27 በሞሮኮ መዲና ራባት ከ33 ሀገራት የተውጣጡ 56 ዳኞች ሲሰጥ የቆየውን ስልጠና የተከታተሉት በዓምላክ ተሰማ እና ተመስገን ሳሙኤል ፈተናውን በብቃት በማለፍ ሰኔ ወር ላይ የሚካሄደውን የአፍሪካ ዋንጫ እንደሚመሩ ታውቋል።

በዓምላክ በተደጋጋሚ ትልልቅ ግምት የሚሰጣቸው አህጉራዊ ውድድሮች እየዳኘ የሚገኝ ሲሆን ይህ ወደ አፍሪካ ዋንጫው ሲጓዝ ለሦስተኛ ጊዜ ነው። ከዚህ ቀደም በ2017 ሁለት፣ በ2015 ደግሞ አንድ በድምሩ 3 የምድብ ጨዋታዎችን መምራት ችሏል።

ሌላው ወደ አፍሪካ ዋንጫው የሚጓዘው ኢንተርናሽናል ረዳት ዳኛ ተመስገን ሳሙኤል ሲሆን በብሔራዊ ቡድን የማጣርያ ጨዋታዎች እና የክለብ ውድድሮች ላይ መዳኘት ይቻል እንጂ ወደ ለአፍሪካ ዋንጫ ሲመረጥ ይህ የመጀመርያው ነው።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡