መቐለዎች ወደ አዲስ አበባ አላመሩም

በነገው ዕለት በኢትዮጵያ ዋንጫ ከፋሲል ከነማ ለመጫወት መርሃግብር የወጣላቸው መቐለ 70 እንደርታዎች እስካሁን ወደ አዲስ አበባ እንዳልተጓዙ ታውቋል።

የሊጉ ቻምፒዮን ጨዋታው ወደሚካሄድበት አዲስ አበባ ያልተጓዘው የውድድሩ ስርዓት አልተከበረም በሚል ነው። በውድድሩ ስነ-ስርዓት ባለሜዳው በዕጣ መታወቅ እያለበት ጨዋታው በገለልተኛ ሜዳ እንዲካሄድ መወሰኑ አግባብ እንዳልሆነ የገለፁት የክለቡ ሥራ አስኪያጅ አቶ ሽፈራው ተክለሃይማኖት ፌዴሬሽኑ መጀመርያ በዕጣ ይለያል ብሎ በደምቡ እንዳሰፈረው በዛ መሰረት መካሄድ እንዳለበት ገልፀዋል።

በመቐለ ውሳኔ ምክንያት የዐፄዎቹ እና ምዓም አናብስት ጨዋታ የመካሄዱ ነገር አጠራጣሪ የሆነ ሲሆን አዳዲስ ለውጦችን ተከታትለን የምናቀርብ ይሆናል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

error: