ለኢትዮጵያ ከ15 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የተጫዋቾች ምልመላ ተጀመረ

በኤርትራ አዘጋጅነት በታሪክ ለመጀመርያ ጊዜ በሚዘጋጀው የሴካፋ ከ15 ዓመት በታች ውድድር ላይ የምትሳተፈው ኢትዮጵያ የተጫዋቾች መረጣ ጀምራለች።

በትላንትናው ዕለት የብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ሆነው የተመረጡት ሰለሞን መካ እና ረዳቶቹ ዛሬ በወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ከ70 በላይ ታዳጊ ተጫዋቾችን የመመልመል ስራ ሲሰሩ ውለዋል። ነገ የመጨረሻ 20 ተጫዋቾችን ለይተው በመምረጥ ከእሁድ ጀምሮ መደበኛ ዝግጅታቸውን የሚጀምሩም ይሆናል።

ቡድኑ ለአምስት ተከታታይ ቀናት ዝግጅት ሲያከናውን ከቆየ በኋላ በቀጣዩ ሐሙስ ወደ ኤርትራ የሚያመራ ሲሆን የመጀመርያ ጨዋታውንም ነሀሴ 10 ከዩጋንዳ ጋር ያከናውናል።

ኢትዮጵያ በምድብ ለ ከዩጋንዳ ፣ ሩዋንዳ ፣ ደቡብ ሱዳን ጋር መደልደሏ ሲታወቅ ውድድሩ ከነሐሴ 9-26 በኤርትራ መዲና አስመራ ይካሄዳል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡