ቻምፒየንስ ሊግ | መቐለ 70 እንደርታዎች የመጨረሻ ልምምዳቸውን አከናውነዋል

ምዓም አናብስት ለነገው ወሳኝ ጨዋታ ዝግጅታቸው አጠናቀዋል።

በቻምፒየንስ ሊግ ሁለተኛ ዙር ነገ 9:00 የኢኳቶሪያል ጊኒው ካኖ ስፖርት አካዳሚን የሚገጥሙት መቐለ 70 እንደርታዎች ዛሬ የመጨረሻው ልምምዳቸው አከናውነዋል። በርከት ባሉ ደጋፊዎች ታጅበው ልምምዳቸው ያከናወኑት መቐለዎች በጉዳት ከዚ ጨዋታ ውጭ ከሆነው ያሬድ ከበደ ውጭ ሙሉ ቡድኑን በዚ ልምምድ ያሳተፉ ሲሆን ለወሳኙ ጨዋታ የሚከተሉት አጨዋወት ላይም ፍንጭ አሳይተዋል።

በመጀመርያው ጨዋታ የአጨራረስ ችግር የነበራቸው መቐለዎች በዛሬው የመጨረሻ ልምምድ አጨራረስ ላይ ያተኮሩ እና ለመስመር አጨዋወት የሚረዱ ልምምዶች አከናውነዋል።

በመጀመርያው ጨዋታ በጠባብ ውጤት የተሸነፉት መቐለዎች በነገው ጨዋታ ከሌላው ጊዜ በተለየ አጥቅተው ይጫወታሉ ሲጠበቅ ከረጅም ጊዜ በኃላ ወደተለመደው የቡድኑ አሰላለፍ (ጠባብ 4-4-2) ይመለሳሉ ተብሎም ይጠበቃል።

ከዚህ በተጨማሪ ቡድኑ ከመጀመርያው ጨዋታ ቋሚ አሰላለፍ ብዙ ለውጥ እንደማያደርግ ሲገመት በተጎዳው ያሬድ ከበደ ምትክ ሳሙኤል ሳሊሶ ወደ ቋሚ አሰላለፍ ይመልሳል ተብሎ ይጠበቃል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡