ባህር ዳር ከተማዎች ሁለተኛ ተጫዋቻቸውን አስፈርመዋል

ሳሙኤል ተስፋዬን ከቅዱስ ጊዮርጊስ በማስፈረም ወደ ዝውውር መስኮቱ የገቡት ባህር ዳር ከተማዎች ሁለተኛ ተጨዋቻቸውን ማግኘታቸውን አስታውቀዋል።

አዲስ የቴክኒክ ክፍል በማዋቀር የዝውውር ገበያውን ዘግይተው የተቀላቀሉት ባህር ዳሮች አሰልጣኛቸው ፋሲል ተካልኝ ያመነባቸውን ተጨዋቾች ወደ ቡድናቸው እየቀላቀሉ ይገኛሉ። ዛሬ ማምሻውንም የኢትዮጵያ ዋንጫ አሸናፊ ከሆነው ፋሲል ከነማ ኤፍሬም ዓለሙን በእጃቸው ማስገባታቸውን አስታውቀዋል። በዘንድሮ የውድድር ዓመት ከፋሲል ከነማ ጋር ጥሩ ጊዜ ያሳለፈው ይህ የአማካይ ተጨዋች ለባህር ዳር ለሁለት ዓመት ግልጋሎት ለመስጠት መስማማቱ ተነግሯል።

ኤፍሬም ቡድኑ ፋሲል ከነማ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ እንዲገባ ወሳኝ ሚና መጫወቱ የሚታወስ ሲሆን ዘንድሮም በወጥ ብቃት ድንቅ ግልጋሎቱን ለውበቱ አባተው ቡድን ሲሰጥ ቆይቷል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡