ጃኮ አራፋት ስለ ታሪካዊ ጎሉ ይናገራል

በ2012 ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ያደገው ወልቂጤ ከተማ ትናንት ፋሲልን በጃኮ አራፋት ጎል 1-0 በማሸነፍ በታሪኩ የመጀመርያ ድል እና ጎል አስመዝግቧል።

ቶጓዊው አጥቂ በወልቂጤ እስካሁን ባለው ቆይታ በሊጉ በሁለት ተከታታይ ጨዋታ ጎል ባያስቆጥርም በትናንትናው ዕለት ስሙን በታሪክ መዝገብ ያሰፈረበትን ጎል በማስቆጠር በወልቂጤ ጎል የማስቆጠር ስራውን ጀምሯል። ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ ስለ ቀጣይ እቅዱ እና ጎል በማስቆጠሩ የተሰማውን ስሜት እንዲህ አጋርቶናል።

ድሉ የፈጠረብህ ስሜት

በመጀመርያ የቡድኑ አባላት አሰልጣኝ ተጫዋቾቻችንን ማመስገን እፈልጋለው። ጥሩ ውጤት ነው ያገኘነው። የሜዳ ላይ ጨዋታ በመሆኑ ውጤቱ ያስፈልገን ነበር። ይህ ዓመት ለወልቂጤ የመጀመርያው የውድድር ጊዜ በመሆኑ ደጋፊዎቻችንን ማስደሰት እንፈልግ ነበር። ይህን ድል በማስመዝገባችን ተደስተናል። በቀጣይም እንዲህ ውጤት እያስጠበቅን ነው መሄድ ነው የምንፈልገው።


በታሪክ የመጀመሪያ ጎል ማስቆጠር

የወልቂጤ የመጀመርያ የፕሪምየር ሊግ ጎል በማስቆጠሬ በጣም ተደስቻለው። አምላኬንም ማመስገን እፈልጋለው። እስካሁን ማመን አልቻልኩም ይህን ታሪካዊ ጎል በማስቆጠሬ። የመጀመርያ ሁለት ጨዋታዎች ላይ ጎል አላስቆጠርኩም ነበር። አሁን ወደ ጎል አግቢነት መመለሴ አስደስቶኛል።

ስለ ቡድኑ ቀጣይ ጉዞ

ቀጣይ ከሰበታ ጋር ነው የምንጫወተው። ሰበታ አዲስ አዳጊ ክለብ ቢሆንም በፕሪምየር ሊጉ ልምድ ያላቸው ብዙ ተጫዋቾች በስብሰቡ ውስጥ ያካተተ ነው። ቀላል ጨዋታ አይሆንም ከባድ ጨዋታ ነው የሚጠብቀን። በአጠቃላይ የዛሬ ጨዋታ ማሸነፋችን የሰጠንን በራስ መተማመን ይዘን እንቀጥላለን።

*ጃኮ አራፋት ለሀገሩ ቶጎ ብሔራዊ ቡድን እና ሜሬላ ክለብ በመቀጠል ለሩሲያው አንዚ ማካቻካላ ጨምሮ ለአስራ ስድስት ክለቦች በዓለም ዙርያ እየዘዋወረ መጫወት ችሏል። ወደ ኢትዮጵያ በ2009 ሀዋሳ ከተማ በመቀላቀል የተሳካ ጊዜን በማሳለፍ በ2010 ወደ ወላይታ ድቻ በኋላም በቀጣይ ዓመት በባህርዳር ከተማ ሲቀላቀል ብዙም የተገመተውን ያህል ቆይታን ሳያደርግ በኢትዮጵያ አራተኛ ክለቡን ዘንድሮ ወልቂጤ ከተማን ተቀላቅሏል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

error: