ህንድ 2020 | አሰልጣኝ ሳሙኤል አበራ ለ24 ተጨዋቾች ጥሪ አቀረቡ

ለዓለም ከ17 ዓመት በትየታች የሴቶች ዓለም ዋንጫ ውድድር ለማለፍ የአሰልጣኝ ቅጥር ያከናወነው የኢትዮጵያ ሴቶች ከ17 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን ለ24 ተጨዋቾች ጥሪ አቅርቧል።

ከቀናት በፊት የብሄራዊ ቡድኑ ዋና እና ረዳት አሰልጣኝ ሆነው በተሾሙት አሰልጣኝ ሳሙኤል አበራ እና ሰርካዲስ እውነቱ የሚመራው ቡድኑ መጋቢት አጋማሽ ላለበት የጅቡቲ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ ዝግጅት ተጨዋቾችን መርጧል።

የተመረጡ ተጨዋቾች ዝርዝር

ግብ ጠባቂዎች

ባንቺአየሁ ደምመላሽ (ባህር ዳር ከተማ)፣ ዓይናለም ሽታ (ድሬዳዋ ከተማ)፣ ፎዚያ ዝናቡ (አዳማ ከተማ)፣ ዓባይነሽ ሄርቄሎ (ሀዋሳ ከተማ)

ተከላካዮች

ፀሀይነሽ በቀለ (ድሬዳዋ ከተማ)፣ ህሊና ኃይሉ (አዳማ ከተማ)፣ ነፃነት ፀጋዬ (አዳማ ከተማ)፣ የምስራች ሞገስ (ወ.ስ. አካዳሚ)፣ ቤቲ በቀለ (ጌዲዮ ዲላ)፣ ቃልኪዳን ተስፋዬ (ጌዲዮ ዲላ)

አማካዮች

ይመችሽ ዘመዴ (ድሬዳዋ ከተማ)፣ ማዕድን ሳህሉ (ድሬዳዋ ከተማ)፣ ፋሲካ መስፍን (አዳማ ከተማ)፣ መሳይ ተመስገን (ኤሌክትሪክ)፣ ሜላት አልሙዝ (ወ.ስ. አካዳሚ)፣ ኝቦኝ የን (ንግድ ባንክ)፣ ዮርዳኖስ በርኸ (መቐለ 70 እንደርታ)፣መዲና ጀማል (አዲስ አበባ ከተማ)

አጥቂዎች

ትዕግስት ወርቁ (ባህር ዳር ከተማ)፣ ፀጋነሽ ወለና (ድሬዳዋ ከተማ)፣ ፋና ዘነበ (ኤሌክትሪክ)፣ ንግስት በቀለ (ወ.ስ. አካዳሚ)፣ አርያት ሁዶንግ (ወ.ስ. አካዳሚ)፣ ሠርክዓለም ባሳ (አርባምንጭ ከተማ)

የተመረጡት ተጫዋቾች ማክሰኞ ታኅሳስ 21 ሪፖርት በማድረግ ዝግጅት እንዲጀምሩ ፌዴሬሽኑ አስታውቋል።


© ሶከር ኢትዮጵያ