“ሁሉን ነገር ትቼ የተቀመጥኩት ለድሬዳዋ ለመጫወት ነው” ረመዳን ናስር

በድሬዳዋ በቅርብ ጊዜያት ከታዩ ባለ ክህሎት የግራ እግር ተጫዋች አንዱ የሆነው ረመዳን ናስር ስላለበት ወቅታዊ ሁኔታ ይናገራል።

ከአምስት ዓመት በላይ ድሬዳዋ ከተማ የቆየውና ከጊዜ ወደ ጊዜ መሻሻል በማሳየት ያለፉትን ሁለት ዓመታት ወሳኝ ተጫዋች መሆኑን እያሳየ የሚገኘው፤ በቅርቡ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጥሪ ቀርቦለት የነበረው ረመዳን ናስር ዘንድሮ ከድሬዳዋ ከተማ ጋር ያለው ኮንትራት ተፈፅሟል። እስካሁን በድሬደዋ ከተማ ለመጫወትም ከስምምነት አልደረስም፤ ምክንያቱ ምንድነው? በሚል ብዙዎች እየጠየቁ መሆኑን ተከትሎ ሀሳቡን መስጠት የፈለገው ረመዳን ይህንን ብሏል።

” ጥሩ ደረጃ ደርሼ ይህንን ክለብ ትቼ እዚሁ የቀረውት ድሬዳዋን ስለምወድ ነው። ሁሉን ነገር ትቼ ቅድሚያ የምሰጠው ለድሬዳዋ ከተማ ለመጫወት ነው። ሆኖም ክለቡ ይህን እያወቀ በተለያዩ ጊዜያት መነጋገር ብችልም እኔ እንዳልፈለኩ ተደርጎ የሚወራው ተገቢ አይደለም። አሁን ለድሬ የመጫወት ከፍተኛ ፍላጎት አለኝ። ችግሩ ያለው እኔ ጋር እንዳልሆነ መላው የድሬዳዋ ማኀበረሰብ እንዲያውቅልኝ እፈልጋለሁ። በክለቡ የማልፈለግ ከሆነ የራሴን አማራጭ እፈልጋለው።”

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!

error: