ዋልያዎቹ ሽንፈት አስተናግደዋል

ዋልያዎቹ ሽንፈት አስተናግደዋል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በሁለት ፍፁም ቅጣት ምት ግቦች በግብፅ ብሔራዊ ቡድን 2ለ0 ተረቷል።

በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ምሽት አራት ሰዓት ሲል ጅማሮውን ባደረገው የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ ሰባተኛ ጨዋታ የግብፅን ብሔራዊ ቡድን የገጠመው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በመጀመሪያ አጋማሽ በተቆጠሩ ሁለት ፍፁም ቅጣት ምት ግቦች ሽንፈት አስተናግዷል።

ገና የጨዋታ ጅማሮ ላይ ኳሶችን ይዘው ወደ ሳጥን በመግባት የዋልያዎችን ተከላካይ መስመር መፈተን የጀመሪት ፈርዖኖቹ በመጀመሪያ አስር ደቂቃዎች ሀለለት አደገኛ ሙከራዎችን አደርገው የዋልያዎቹ የግብ ዘብ አቡበከር ኑራ በግሩም ሁኔታ አምክኖባቸዋል።

የጨዋታ ብልጫ የነበራቸውን በአማዛኙ የተቃራኒ ቡድን ሜዳ ክፍል ላይ ሲያዘውትሩ የነበሩት ፈርዖኖቹ በ17ኛው ደቂቃ ዳግም ያለቀ ኳስ አግኝተው አቡበከር ኑራ መልሶባቸው የማዕዘን ምት ሲሀሸን ከማዕዘን የተሻማውት ኳስ ኦማር ማርሙሽ በግንባሩ ገጭቶ ያደረገውን ሙከራ ዳግም የግቡ ዘብ አውጥቶባቸዋል። እንዲሁም በ20 ደቂቃ ላይ ከሳጥን ውጪ ሆነው ያደረጉትን አደገኛ ሙከራ የግቡ ቋሚ ብረት ይመልስባቸው እንጂ ቀዳሚ ለመሆን የቀረቡበት ሌላኛው ሙከራ ነበር።

በኳስ ቁጥጥር ብልጫ የተወሰደባቸው ዋልያዎቹ በ28ኛው ደቂቃ ላይ የመጀመሪያውን ሙከራ አድርገዋል፣ አቡበከር ኑራ በረጅሙ የለጋውን ኳስ በረከት ደስታ አግኝቶ ከከነዓን ማርክነህ ጋር ተቀባብለው ከሳጥን ውጪ የመታውን ኳስ ግብ ጠባቂው በቀላሉ ተቆጣጥሮታል።

ጨዋታው 38ኛው ደቂቃ ላይ ሲደርስ የመጀመሪያ ግብ የሆነበት ፍፁም ቅጣት ምት የግብፅ ብሔራዊ ቡድን አግኝቷል። ኳስ ይዘው ወደ ሳጥን በሚገቡበት ቅፅበት ሱሌይማን ሀሚድ በሰረው ጥፋት ፍፁም ቅጣት ምት አግኝተው መሐመድ ሳላህ ወደ ግብነት ቀይሮ 1ለ0 እንዲሆኑ አስችሏቸዋል።

አጋማሹ ሊጠናቀቅ ጭማሪ በታየው ላይ ሳጥን ውስጥ በተፈጠረ በእጅ ንክኪ ዳግም ፍፁም ቅጣት ምት ለግብፅ ብሔራዊ ቡድን ተሰጥቶ የማንችስተር ሲቲው ተጫዋቾ ኦማር ማርሙሽ ከመረብ ጋር አገናኝቶ የመጀመሪያ አጋማሽ በግብፅ ብሔራዊ ቡድን 2ለ0 መሪነት ተገባዶ ወደ መልበሻ ክፍል አምርተዋል።

ጨዋታው በሁለተኛው አጋማሽ ሲቀጥል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከመጀመሪያ አጋማሽ አንፃር ተጠናክሮ በመግባት ወደ ፊች የመሄድ አዝማሚያ ቢያስመለከትነም ጨንከር ያለ ሙከራ ማድረግ አልተቻላቸውም። 60ኛው ደቂቃ ላይ ለይደር ሸረፋ ርቀት ላይ ሆኖ ያደረገው ሙከራ በግቡ አናት በኩል ያለፈበት አጋጣሚ ይጠቀሳል። ጠንከር ብለው ወደፊት እየሄዱ ሶስተኛው ሜዳ ክፍል ማዘውተር የቀጠሉት ዋልያዎቹ ከስላሰዎቹ እስከ ሰባዎቹ መጀመሪያ ድረስ ባሉት ደቂቃዎች ግልፅ የግብ ማግባት ሙከራ ቢያስመለከቱም የተሻለ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ለመመለከት ችለናል።

ዘለግ ላለ ደቂቃ የግብ ማግባት ሙከራዎችን ማልረግ ያልቻለው የግብ ብሔራዊ ቡድን 76ኛው ደቂቃ ላይ ለሶስተኛ ግብ የቀረበ ሙከራ አድርገው በጨዋታው በርከት ያሉ ኳሶችን ወደ ግብነት እንዳይቀየሩ በጥሩ ቅልጥፍና ኳሶችን ሲመልስ የነበረው የግቡ ዘብ እንዴትም መልሶባቸዋል። እንዲሁም በ79ደቂቃ ላይ ሌላኛውን ያለቀ ኳስ መመለስ ችሏል።

ዋልያዎቹ 82ኛው ደቂቃ ላይ ያደረጉት አደገኛ ሙከራ ሲታወስ የቆመ ኳስ ተሻምቶ ሳጥን ውስጥ ሆነው ያደረጉትን ሙከራ የፈርዖኖቹ ግብ ጠባቂ እንዴትም ሎኖ አድኖባቸዋል። ጨዋታውም በመጀመሪያ አጋማሽ በተቆጠሩ ሁለት ፍፁም ቅጣት ምት ግቦች በግብፅ ብሔራዊ ቡድን አሸናፊነት ተጠናቋል።