የሱራፌል ዳኛቸው ዝውውር ተጠናቋል

የሱራፌል ዳኛቸው ዝውውር ተጠናቋል

ቀደም ብለው አጥቂው አቤል ያለውን የግላቸው ያደረጉት ሲዳማ ቡናዎች ቡድናቸውን ማጠናከር ተያይዘውታል

ከአንድ ዓመት ከዘጠኝ ወር የአሜሪካ ቆይታ በኋላ ወደ ሀገር ቤት ተመልሶ ስሙ በርከት ካሉ ክለቦች ጋር ሲያያዝ የቆየው አማካዩ ሱራፌል ዳኛቸው ወደ ሲዳማ ቡና ማምራቱ እርግጥ ሆኗል። ከቀናት በፊት ባጋራናቹህ ዜና አማካዩ ሲዳማ ቡናን ለመቀላቀል ከጫፍ መድረሱን መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን ዛሬ ደግሞ ሊጉን በመምራት ላይ የሚገኙት ቡናማዎቹ በቅርብ ዓመታት በክለብ እና በብሔራዊ ቡድን ደረጃ በጥሩ ብቃት የተጫወተው የቀድሞ የአዳማ ከተማ፣ ፋሲል ከነማና ሎዶን ዩናይትድ ተጫዋች የግላቸው ማድረጋቸው ተረጋግጧል።