ሲዳማ ቡና ከሁለት ተጫዋቾች ጋር ተለያይቷል

ሲዳማ ቡና ከሁለት ተጫዋቾች ጋር ተለያይቷል

አመሻሹን ጠንከር ያሉ ዝውውሮችን የፈፀመው የሊጉ መሪ አሁን ደግሞ ከሁለት ተጫዋቾቹ ጋር መለያየቱ ተሰምቷል

በዘንድሮ የውድድር ዓመት በሊጉ እና በኢትዮጵያ ዋንጫዎች ላይ ጠንከር ያለ ተሳትፎ እያደረገ የሚገኛው እና እራሱን ለማጠናከር ከሰዓታት በፊት አቤል ያለውን እና ሱራፌል ዳኛቸውን የግሉ ያደረገው የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ከሁለት ተጫዋቾች ጋር መለያየቱ ታውቋል።

የመጀመርያው ተጫዋች አማካይ አበባየሁ ሀጂሶ ሲሆን ከአሳዳጊው ክለብ ወላይታ ድቻ ሲዳማ ቡናን ተቀላቅሎ ያለፈውን አንድ ዓመት ቡድኑን ያገለገለ ሲሆን አሁን በስምምነት ተለያይቷል። ሌላኛው ከቡድኑ ጋር የተለያየው አጥቂው ተመስገን መንገሻ ነው፤ ከዚህ ቀደም በአርባምንጭ ከተማ ፣ሰሜን ሸዋ ደብረብርሀን ተጫውቶ በያዝነው ዓመት ሲዳማ ቡና በመቀላቀል ያለፉትን ስድስት ወራት ቡድኑ ሲያገለግል ከቆየ በኋላም አሁ በስምምነት መለያየቱ ታውቋል።