የቡናማዎቹ ዋና አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ምን አሉ

የቡናማዎቹ ዋና አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ምን አሉ

👉 ” ቡድን ሻምፕዮን ማድረግ ይጠበቅብኛል።

👉 “አትጠራጠሩ ጥሩ ውጤት እናመጣለን

👉 ” ይህን ታሪካዊና ትልቅ ክለብ ለማሰልጠን ሁሉም ይጓጓል።

በአሁኑ ሰዓት በስካይ ላይት ሆቴል የቀጣዮ ሁለት ዓመት የኢትዮጵያ ቡና ዋና አሰልጣኝ ገብረመድን ሀይሌ በይፋ የፊርማ ስነ ሥርዓቱ እየተከናወነ ይገኛል። በዚህ ፕሮግራም ላይ ዋና አሰልጣኙ የመግቢያ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በዋናነት ያነሷቸውን ነጥብ እንደሚከተለው አቅርበንላችኋል።

“ከ16 ዓመታት በኃላ ዳግም ስለተገናኘን ደስ ብሎኛል ፤ ኢትዮጵያ ቡናን እንዳሰለጥን ታምኖብኝ ይህ ዕድል ስለተሰጠኝ አመሠግናለሁ። ኢትዮጵያ ቡናን ማሰልጠን የማይፈልግ አሰልጣኝ የለም ፤ ይህን ታሪካዊና ትልቅ ክለብ ለማሰልጠን ሁሉም ይጓጓል። የሚያሰለጥነው ደግሞ አንድ ሰው ነው። ክለቡ ይህን ኃላፊነት ሲሰጠኝ ቡድኑን ወደ ከፍታ ይመራልናል ብሎ ነው ስለዚህ እኔን ይሄን ቡድን ሻምፒየን ማድረግ ይጠበቅብኛል። በዓመት በተንሹ በአማካይ በጨዋታ ሁለት ነጥቦች አግኝተን 67(68) ነጥብ ካገኘን ሊጉን ማሸነፍ እንችላለን። ይህን ለማድረግ አስፈላጊውን ዝግጅት ከ20 ቀን በኃላ በይፋ ዝግጅት እንጀምራለን ፤ 8 ውል ያላቸው ተጫዋቾች አሉን ሌሎች ጥራት ያላቸው ተጫዋቾች ከወጣቶች ጋር አጣምረን ጠንካራ ቡድን ለመስራት እንሞክራለን ይህ ደግሞ በግሌ ብቻ ሳይሆን የጋራ ጥረት ይጠይቃል በተለይም ደግሞ 12ኛ ተጫዋች ከሆነው ደጋፊያችን ጋር አንድ በመሆን በአዲሱ ዓመት ጥሩ ውጤት እናመጣለን አትጠራጠሩ ብለዋል። ”

ከመገናኛ ብዙኃን ለተነሱ ጥያቄዎች የሚሰጡትን ምላሽ በቀጣይ ይዘን እንመጣለን።