ቅዱስ ጊዮርጊስ የሁለት ተጫዋቾችን ዝውውር አጠናቋል።

ለ2019 የውድድር ዓመት ቡድኑን ለማጠናከር እንቅስቃሴ እያደረጉ የሚገኙት ቅዱስ ጊዮርጊሶች የሁለት ተጫዋቾችን ዝውውር ማጠናቀቃቸውን ክለቡ ይፋ አድርጓል። ክለቡን የተቀላቀሉትም ብሩክ እንዳለ እና ተመስገን ብርሃኑ ናቸው።
አማካይ ብሩክ እንዳለ ከዚህ ቀደም በገላን ከተማ ሲጫወት የምናውቀው እና በ2016 ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር የሊጉን ዋንጫ ያነሳ ሲሆን ዘንድሮ ከወልዋሎ ጋር የኢትዮጵያ ዋንጫ ማንሳቱ ይታወቃል።
ሌላኛው የፈረሰኞቹ ፈራሚ ፈጣኑ አጥቂ ተመስገን ብርሃኑ ነው የእግርኳስ ሕይወቱን በሀዲያ ሆሳዕና ከታዳጊ እስከ ዋናው ቡድን ያደረገ ሲሆን አሁን ሁለተኛ ክለቡ ይሆን ዘንድ ቅዱስ ጊዮርጊስን መርጧል። ተጫዋቾቹም የሕክምና ምርመራቸውን አጠናቅቀው በይፋ ፊርማቸውን ያኖራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

