👉 “ስታዲየም ለመገንባት ዲዛይን ጨርሰናል በአጠቃላይ ወደ ስምንት ቢልየን ይፈልጋል..
👉 “እንደሚባለው “ደሃ” ክለብ ሳይሆን ብዙ ፀጋዎች ያሉት ሀብታም ክለብ ነው…” እስራኤል ደገፉ (ዶ/ር)

በስካይ ላይት ሆቴል እየተካሄደ ባለው የኢትዮጵያ ቡና የቀጣይ ዓመት ዕቅድ እና በአሰልጣኝ ገብረመድን ሹመት ዙርያ በስፋት ከመገናኛ ብዙሀን ጥያቄዎች እየተነሱ ይገኛል በዚህ ዙርያ ከክለቡ አስተዳደር እና ተያያዥ ጉዳዮች በተመለከተ ለተነሱ ጥያቄዎች የክለቡ ፕሬዝደንት እስራኤል ደገፉ (ዶ/ር) የሰጡትን ምላሽ እንዲህ አቅርበነዋል።
የክለቡ የፋይናስ ዘላቂነት ?
“በዋነኝነት መስራት የምንፈልገው ዘለቄታዊነት ላይ ነው ፤ ቡድኑ በጥናት እየተመራ ከተረጂነት ወደ ረጂነት ማሸጋገር ነው።ያስጠናነው ጥናት በቦርድ ፀድቆ በዘመናዊ መዋቅር ለመንቀሳቀስ ወደ ትግበራ ገብተናል አሁን ላይ ዘመናዊ መዋቅር የተላበሰ እንዲሆን ባለሙያዎችን እየቀጠርን እንገኛለን።”
የስታዲየም ግንባታ ?
“ያለንን ስታዲየም ለመገንባት ዲዛይን ጨርሰናል በአጠቃላይ ወደ ስምንት ቢልየን ይፈልጋል ይሄንንም ወደ ስራ ለማስገባት እየሰራን እንገኛለን።”
የክለቡ አቅም ?
“ኢትዮጵያ ቡና ብዙ ሪሶርሶች ያሉት ክለብ ነው እንደሚባለው “ደሃ” ክለብ ሳይሆን ብዙ ፀጋዎች ያሉት ሀብታም ክለብ ነው” “ከኢትዮጵያ ቡና ባለቤቶች ቀዳሚ የሆነውን የቡና አምራች አርሷደሮችን በቀጥታ ለቡድኑ ድጋፍ የሚያደርግበት አግባብ አልነበረም አሁን ግን ያንን ለማድረግ ስራዎችን ጀምረናል።”

