ኢትዮጵያ ቡና በዋና አሰልጣኙ ቅጥር እና በክለቡ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙርያ በስካይ ላይት ሆቴል መግለጫ እየሰጠ ይገኛል

ኢትዮጵያ ቡና በዋና አሰልጣኙ ቅጥር እና በክለቡ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙርያ በስካይ ላይት ሆቴል መግለጫ እየሰጠ ይገኛል

👉 ” ኢትዮጵያ ቡና ወደ አዲስ ገፅታ ከፍታ ለማሸጋገር ትልቅ እመርታ ነው” ዶክተር እስራኤል ደገፉ

 

ኢትዮጵያ ቡና በቅርብ አዲስ በሾሙት አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ ቅጥር ዙርያ እና በክለቡ ወቅታዊ ጉዳዮች በተመለከተ ዛሬ በማለዳው ላይ ስካይ ላይት ሆቴል የቡናና ሻይ ምክትል ዳሬክተር አቶ ሻፊ ኡመር ፣ የቡና ሻይ ባለስልጣና የልማት ዘርፍ አቶ ታጋይ ኑሩ፣ አቶ ደሳለኝ ዳኑ እንዲሁም አዲሱ ክለቡ ፕሬዝደንት ዶክተር እስራኤል ደገፉ እና ሌሎች የክለቡ የቦርድ አባላቶች የደጋፊ ማህበራት አመራሮች በተገኙበት ለመገናኛ ብዙኀን ማብራሪያ ተሰጥቷል።

በጋዜጣዊ መግለጫውም የክለቡ ፕሬዝደንት እስራኤል ደገፉ (ዶክተር) “የዛሬዋ ቀን የተለየች ናት ኢትዮጵያ ቡናን ወደ አዲስ ገፅታ ከፍታ ለማሸጋገር ትልቅ እምርታ ነው። አሰልጣኝ ገብረመድህን በኢትዮጵያ እግርኳስ የተከበረ ስም ያለው ብዙ ዘመናት ትልቅ አስተዋፆኦ ያደረገ የሊጉን ዋንጫዎች ያነሳ ትልቅ ኢትዮጵያዊ አሰልጣኝ ነው ። የወደፊቱን ኢትዮጵያ ቡና አዲስ ገፅታ፣ ለውጥ ሀይልን ለመገንባት ወደ እኛ እንዲቀላቀል ስንጠራው በሙሉ ፍቃደኝነት ነው የመጣው። ኢትዮጵያ ቡና ያለፉትን ሃምሳ ዓመት በእግርኳሱ ኢንዱስትሪ እንዲነቃቃ እንዲቀየር በማድረግ ትልቅ አሻራ ጥሎ ያለፈ ክለብ ነው። የአዲሱ የኢትዮጵያ እመርታን ሊያበሰር ከጎናችን ይገኛል። በቀጣይም ኢትዮጵያ ቡና ይህን ተልኮ ይዞ ይንቀሳቀሳል”በማለት ተናግረዋል

በቀጣይ አሰልጣኝ ገብረመድን ሀይሌ በቅጥራቸው ዙርያ እና ሌሎች የሚሰጧቸውን አስተያየቶች ይዘን የምንመለስ ይሆናል።