ከነገሌ አርሲዎች ጋር የስድስት ወር ቆይታ የነበረው የመስመር አጥቂው ወደ ሌላ ክለብ አምርቷል

በኢትዮጵያ ቡና ታዳጊ ቡድን ተገኝቶ በገላን ከተማ፣ በኢትዮጵያ መድን፣ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እንዲሁም በዘንድሮ ዓመት ስድስት ወሩን ለመቐለ 70 እንድርታ እና ለነገሌ አርሲ መጫወት የቻለው የመስመር አጥቂው ኪቲካ ጅማ ለባህር ዳር ከተማ ለመጫወት መስማማቱ ታውቋል። የመስመር አጥቂውን ከማስፈረማቸው አስቀድሞ የሽመልስ በቀለን ዝውውር ያጠናቀቁት ባህር ዳሮች ቡድናቸውን ለማጠናከር ተጨማሪ ዝውውሮች ይፈፅማሉ ተብሎ ይጠበቃል።

