የሽመልስ በቀለ ማረፊያ ታውቋል

የሽመልስ በቀለ ማረፊያ ታውቋል

ባለፉት ሁለት ዓስርት ዓመታት ከታዩ ምርጥ አማካዮች አንዱ የሆነው ሽመልስ በቀለ ወደ የጣና ሞገዶቹ ለመቀላቀል ተቃርቧል

ከሀዋሳ ከተማ ጋር ለሁለት ዓመታት ለመቆየት የሚያስችል የውል ስምምነት ቢኖረውም በቅርቡ የመልቀቂያ ደብዳቤ አስገብቶ ከሐይቆቹ ጋር በስምምነት የተለያየው ሽመልስ በቀለ መዳረሻው ባህር ዳር ከተማ ለመሆን መቃረቡን ሶከር ኢትዮጵያ
ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው ታማኝ ምንጮቿ አረጋግጣለች።

የእግርኳስ ህይወቱን በኮረም ሜዳ የጀመረው አማካዩ ሽመልስ በቀለ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጨምሮ በክለብ ደረጃ በሀዋሳ ከተማ፣ በቅዱስ ጊዮርጊስ በማስከተል ከሀገር ውጭ ለሱዳኑ ኤል ሜሪክ እና ለሊብያው አል ኢትሀድ እንዲሁም ድፍን አስር ዓመታት ወደ ቆየበት ግብፅ በማቅናት የክለቡ የምንጊዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ በሆነበት እና በአምበልነት ያገለገለበትን ፔትሮጀት ጨምሮ በኤል ጎውና ፣ ምስር አል መቃሳ እና ኤን ፒፒ አይ በመጫወት ከኢትዮጵያ ውጭ የእግርኳስ ህይወቱን ካጠናቀቀ በኋላ ወደ ሀገር ቤት በመመለስ ለመቻል እንዲሁም ወደ ቀድሞ ክለቡ ሀዋሳ ከተማ ለአንድ ዓመት ሲጫወት ቆይቶ አሁን ደግሞ ወደ ጣና ሞገዶቹ ለማቅናት መስማማቱ እርግጥ ሆኗል።