ከድሬዳዋ ከተማ ጋር በግሉ ጥሩ እንቅስቃሴ ያደረገው ፈጣኑ የመስመር ተከላካይ ነገሌ አርሲን ለመቀላቀል ተስማምቷል።

ለቀጣይ የውድድር ዓመት ራሳቸውን ለማጠናከር ጠንከር ያሉ ዝውውሮችን እያከናወኑ የሚገኙት ነገሌ አርሲዎች አሁንም ወደ ገበያው በመግባት ፈጣኑን የመስመር አጥቂ ጀሚል ያዕቆብን ለማስፈረም ተስማምተዋል።
በጅማ አባቡና፣ ጅማ አባ ጅፋር ፣ አዳማ ከተማ እና ያለፉትን ዓመታት በድሬዳዋ ከተማ በግሉ ጥሩ እንቅስቃሴ ያደረገ ሲሆን አሁን ለሁለት ዓመት ለመቆየት ወደ ነገሌ አርሲ ለማምራት ተስማምቷል።

