የሊጉ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ ከዋልያዎቹ ስብስብ ውጭ ሆኗል

የሊጉ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ ከዋልያዎቹ ስብስብ ውጭ ሆኗል

ባሳለፍነው ዓመት የሊጉን ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪነት ያሳካው አጥቂ ከዋልያዎቹ ስብስብ መቀነሱ ታውቋል

በአሰልጣኝ ዮሐንስ ሳሕሌ የሚመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድነ በቀናቶች ልዩነት ከሱዳን እና ከሴኔጋል ጋር ለሚኖረው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታዎች ዝግጅቱን ከጀመረ ሰነባብቷል ትናንት ካርሎስ ዳምጠው እና በረከት ሳሙኤልን ወደ ስብስቡ የቀላቀለው ቡድኑ አሁን ደግሞ አንድ ተጫዋች መቀነሱ ታውቋል። ባሳለፍነው ዓመት ከናትናኤል ዳንኤል ጋር የሊጉን ከፍተኛ ጎል አግቢነትን በጣምራ ማሳካት የቻለው የዐፄዎቹ አጥቂ ታምራት እያሱ ደግሞ ከብሔራዊ ቡድኑ መቀነሱን ለክለቡ በተላከ ደብዳቤ ማረጋገጥ ችለናል።