ትናንት እና ዛሬ በስብስባቸው ላይ ለውጦችን እያደረጉ የሚገኙት አሠልጣኝ ዩሐንስ ሌላ ተጫዋች ቀንሰዋል።


ዘለግ ላሉ ጊዜያት ብሔራዊ ቡድኑን እያዘጋጁ የሚገኙት የዋልያዎቹ አሠልጣኝ ዮሐንስ ሳሕሌ ትናንት ደግፌ ዓለሙን ዛሬ ደግሞ አጥቂው ታምራት እያሱን የቀነሱ ሲሆን አሁን በደረሰን መረጃ መሰረት ደግሞ የቅዱስ ጊዮርጊሱ የመስመር ተጫዋች ፀጋአብ ግዛውም ከስብስቡ እንደተቀነሰ ለማወቅ ችለናል።
በቅዱስ ጊዮርጊስ ታዳጊ ቡድን አጥቂ በመሆን ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴ አሳይቶ የነበረው ፀጋ በኋላም ወደ ሀድያ በማቅናት ያለፉትን ሁለት ዓመታት በነብሮቹ ቤት ቆይታ አድርጎ ክረምት ላይ ዳግም ወደ አሳዳጊ ቤቱ ለመጫወት የሁለት ዓመት ስምምነት ያደረገ ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜም የብሔራዊ ቡድን ጥሪ ደርሶት ከቡድኑ ጋር ዝግጅት ሲሰራ ነበር። በዛሬው ዕለት ግን ከስብስቡ መቀነሱ ታውቋል።

