አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳሕሌ ለሁለት ተጫዋቾች ጥሪ አደረጉ

አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳሕሌ ለሁለት ተጫዋቾች ጥሪ አደረጉ

ራሱን ከብሔራዊ ቡድን አግልሎ የነበረውና በአህጉራዊ ውድድር የደመቀው ተጫዋች የዋልያዎቹ ጥሪ ደረሳቸው።

በክረምቱ የዝውውር መስኮት ወላይታ ድቻን ለቆ ወደ ወልዋሎ በማምራት በመጀመሪያዎቹ ሁለት የአህጉራዊ ውድድር ጨዋታዎች ሦስት ግቦችን ያስቆጠረው አጥቂው ካርሎም ዳምጠው እና ከዓመታት የሀዋሳ ከተማ ቆይታው ወደ ወልዋሎ ያመራው ተከላካዩ በረከት ሳሙኤል ለመጀመሪያ ጊዜ ሀገራቸው እንዲያገግሉ በአሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ጥሪ ቀረበላቸው።

ተከላካዩ በረከት ሳሙኤል ከዚህ ቀደም በወቅቱ የዋሊያዎቹ አሠልጣኝ ጨምሮ በቀደሙት ጊዜያት ከብሔራዊ ቡድን ምርጫ መዘለሉን በመጥቀስ ከብሔራዊ ቡድኑ ራሱን ማግለሉ በይፋዊ ቃለምልልስ ለሶከር ኢትዮጵያ ገልፆ የነበረ ሲሆን አሁን ሀገሩን ለማገልገል በቅቷል።

አጥቂው ካርሎስ ዳምጠው ደግሞ በትናንትናው ዕለት ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር በነበረው ቆይታ ሀገሩን ማገልገል የሁልጊዜ ምኞቱ እንደሆነ ገልፆ አንድ ቀን ይሳካል ብሎ እንደሚያምን መግለፁ የሚታወስ ሲሆን አሁን ለመጀመሪያ ጊዜ ከብሔራዊ ቡድኑ ጥሪ ደርሶታል።

ሁለቱም ተጫዋቾች ነገ ከሰዓት ብሔራዊ ቡድኑ የሚገኝበት ሀዋሳ እንዲገኙም ተገልጿል።