በርበሬዎቹ የተከላካይ አማካይ አስፈርመዋል

በርበሬዎቹ የተከላካይ አማካይ አስፈርመዋል

አዲስ አዳጊዎቹ ሴኔጋላዊውም ተጫዋች ለማስፈረም ከስምምነት ደርሰዋል

ከትናንት በስቲያ ኮንኮኒ ሀፊዝ እና ካሌብ አማንክዋህን ለማስፈረም የተስማሙት ሀላባ ከተማዎች አሁን ደግሞ ሴኔጋላዊ የተከላካይ አማካይ ለማስፈረም መስማማታቸውን አውቀናል። ቡድኑን ለመቀላቀል የተስማማው ተጫዋች ደግሞ 1.82 ሜትር የሚረዝመው የ28 ዓመቱ ሳምባ ሴክ ሲሆን ተጫዋች ከዚህ ቀደም ለሀገሩ ክለቦች ዩ ኤስ ጎሪኔ እና ኦዋካም መጫወት ችሏል።