ከሀድያ ሆሳዕና ጋር ጥሩ ቆይታ የነበረው አማካይ ሙሴ ከበላ ወደ ሀዋሳ ከተማን ለመቀላቀል ተስማምቷል።
በአሰልጣኝ ተመስገን ዳና የሚመሩት ሀዋሳ ከተማዎች ከደቂቃዎች በፊት የመስመር የተከላካይ ብረክ ታደለ እና ግብጠባቂ ምንተስኖት ጊንቦን ውል በማራዘም እና የአዲስ ፈራሚው ቃለአብ ውሸት ዝውውር ማጠናቀቃቸው ይታወሳል። አሁን ደግሞ አማካይ ሙሴ ከበላን ሁለተኛ ፈራሚያቸው ለማድረግ ተስማምተዋል።
በኢትዮጵያ ቡና፣ በአዳማ ከተማ ፣ በኢትዮ ኤሌክትሪክ እና በሀድያ ሆሳዕና ቆይታ የነበረው ሙሴ በዚህ ዓመት ባሳየው ድንቅ አቋም ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለመጀምርያ ጊዜ መጠራቱ ይታወቃል። አሁን መዳረሻውን ሀዋሳ ከተማ ለማድረግ ለሁለት ዓመት ተስማምቷል።

