በአሰልጣኝ በፀሎት ልዑልሰገድ የሚመሩት ኢትዮጵያ ንግድ ባንኮች የሁለት ወሳኝ ተጫዋቾቻቸውን ማቆየት ችለዋል።

ወደ ዝውውሩ ዛሬ በመግባት ሙሉቀን አዲሱን እና እዩብ ተስፋዬን በማስፈረም እንዲሁም የግብ ጠባቂ አማኑኤል ደስታ ፣ ብሩክ ብፁአምላክ ፣ አቤኔዜር ተክሉ እና ዮሐንስ ኪዳኔ ውል ያራዘሙት የኢትዮጵያ ንግድ ባንኮች አሁን ደግሞ የተስፋዬ ታምራት እና የቢንያም ካሳሁንን ውል ማራዘማቸው ታውቋል።
በኢትዮጵያ ቡና ታዳጊ እና ዋናው ቡድን በመጫወት የእግር ኳስ የጀመረው ቢንያም በገላን ከተማ ከተጫወተ በኋላ ኢትዮጵያ መድን እና ኢትዮ ኤሌክትሪክን በተለያዩ ዓመታት ወደ ፕሪምየር ሊጉ ሲያድጉ የቡድኖቹ አባል መኖሩ ሲታወስ አሁን ደግሞ ለተጨማሪ ሁለት ዓመታት በኢትዮጵያ ንንግድ ባንክ ለመቆየት ተስማምቷል።
ሌላኛው በቡድኑ ለመቆየት የተስማማው ተጫዋች የግራ መስመሩ ተጫዋቹ ታምራት ተስፋዬ ነው። በወላይታ ድቻ፣ ኢትዮጵያ መድን ፣ በባህር ዳር ከተማ፣ ከተጫወተ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በመምጣት የሊጉን ዋንጫ ማንሳት የቻለው ተጫዋቹ አሁን ደግሞ ለተጨማሪ ዓመት በሀምራዊ ለባሾቹ ጋር የሚቆይ ይሆናል።

