ሐይቆቹ የሁለት ተጫዋቾች ውል ለማራዘም ከስምምነት ደርሰዋል

የሁለት ታዳጊዎችን ውል በማሳደስ ወደ ዝውውር ገብቶ ቃለአብ ውብሸትን፣ ሙሴ ከበላን እና የቀድሞ ተጫዋቹን ብሩክ በየነን የግሉ ያደረገው ሀዋሳ ከተማ የሁለት ተጫዋቾች ውል ለማራዘም ከስምምነት ደርሷል። የወጣት ቡድኑ ፍሬ የሆኑት የአማካይ ስፍራ ተጫዋች ናትናኤል ሻጋሞ እና የመስመር ተከላካዩ ሲሳይ ጋቾ ደግሞ ከአሳዳጋቸው ክለብ ጋር ለመቆየት መስማማታቸውን የሁለት ዓመት ውል እንዳሰሩም ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

