ፈረሰኞቹ ለታዳጊዎች ከፍተኛ የደሞዝ ጭማሪ አደረጉ

ፈረሰኞቹ ለታዳጊዎች ከፍተኛ የደሞዝ ጭማሪ አደረጉ

ቅዱስ ጊዮርጊስ ሰጪ እንቅስቃሴ ላሳዮት ውል ያላቸው ተስፈኛ ተጫዋቾች የደሞዝ ጭማሪ አደረገ

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ብዙ ታዳጊዎችን ወደ ዋናው ቡድን በማሳደግ ውጤታማ መሆን ከቻሉት ክለቦች መካከል ቅዱስ ጊዮርጊስ አንዱ ነው። ዘንድሮ በርከት ያሉ የተስፋ ቡድን ተጫዋቾቹን ወደ ዋና ቡድን ያሳደገው ክለቡ ውል ያላቸው በቢጫ እና በአረንጓዴ ቴሴራ እየተጫወቱ ለሚገኙት ለሁሉም ተጫዋቾቹ በሚባል ደረጃ ከፍተኛ የደሞዝ ጭማሪ እንዳደረገ ሰምተናል።

ከሁለት ሺህ አምስት መቶ እስከ ሃያ ሺህ በብር ደሞዝተኛ የነበሩትን ታዳጊዎቹን ደሞዛቸው ከመቶ ሺህ ብር እስከ መቶ ሃምሳ ሺህ ብር ከፍ በመድረግ ታዳጊዎቹን የበለጠ እንዲተጉ ለማድረግ የደሞዝ ጭማሪው መደረጉን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።