ፍፁም ጥላሁን ከሀምራዊ ለባሾቹ ጋር ለመስማማት ተቃርቧል

ፍፁም ጥላሁን ከሀምራዊ ለባሾቹ ጋር ለመስማማት ተቃርቧል

ከፈረሰኞቹ ጋር እንደማይቀጥል ዕርግጥ የሆነው የመስመር አጥቂው ማረፊያው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሊሆን ከጫፍ ደርሷል።

ከጥቂት ቀናት በፊት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እና ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ድንቅ አቋሙን ሲያሳይ የከረመው የመስመር አጥቂው ፍፁም ጥላሁን በፈረሰኞቹ ቤት ውሉን ለማራዘም ያደረገው ድርድር እንዳልተሳካና በክለቡ እንደማይቀጥል መግለፃችን ይታወሳል። ከፈረሰኞቹ ጋር እንደማይቀጥል ከተረጋገጠ በኋላም በብዙ የሊጉ ክለቦች ሲታደን ቆይቶ በስተመጨረሻ ቀጣይ ማረፊያው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለመሆን ከጫፍ እንደደረሰ ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው ታማኝ ምንጮቻችን አረጋግጠናል።

ከዚህ ቀደም በቅዱስ ጊዮርጊስ ታዳጊ ቡድን ቀጥሎም በኢትዮጵያ ቡና በተስፋ እና በዋናው ቡድን ከተጫወተ በኋለ ለአዲስ አበባ ከተማ ፣ ለባህር ዳር ከተማ ያለፉትን ሁለት ዓመታት ደግሞ ቅዱስ ጊዮርጊስን በማገልገል ስምንት ጎሎችን በማስቆጠር ጥሩ የውድድር ዓመት ያሳለፈ ሲሆን አሁን ደግሞ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለሁለት ዓመት ለመጫወት ተስማምቷል።