አዲስ አዳጊዎቹ ወደ ስብስባቸው አንድ ተከላካይ መቀላቀል ችለዋል።

በአሰልጣኝ ማቲዮስ ለማ የሚሰለጥኑት አዲስ አዳጊዎቹ ጋሞ ጨንቻዎች ወደ ዝውውሩ ከገቡበት ጊዜ ጀምሮ የተለያዩ አዳዲስ ተጫዋቾችን በማምጣት እና የነባር ተጫዋቾችን ውል በማራዘም ላይ ይገኛሉ። አሁን ደግሞ ተከላካይ ትኩሱ ጌታቸውን ማስፈረማቸው ታውቋል።
የመሐል ተከላካዩ ከዚህ ቀደም በቡሌ ሆራ ፤ በከፍተኛ ሊጉ በእንጅባራ ከተማ እና በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በንብ ክለብ ጥሩ ጊዜ ያሳለፈ ሲሆን አሁን ለአዲስ አዳጊዎቹ ጋሞ ጨንቻ ለመጫወት ተስማምቷል።

